ታንዛኒያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 1 ለ 0 አሸነፈች

ታንዛኒያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – ዛሬ ከሰዓት ታንዛኒያ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባገናኘው ጨዋታ ታንዛኒያ ድል ቀንቷታል፡፡

በዚህም መሠረት ታንዛኒያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ መቻሏን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የታንዛኒያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ማለዳ ባህር ዳር የደረሰ የመጨረሻው የልዑክ ቡድን መሆኑ ይታወሳል፡፡