የሚኒስቴሩ አመራርና ሰራተኞች በወላይታ ዞን የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎችን አስጀመሩ


ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) –
የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በወላይታ ዞን በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎችን አስጀመሩ፡፡
የፌዴራል የመንግሥት ተቋማት እያካሄዱ በሚገኘው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በአረንጓዴ አሻራ ልማት፣ የከተማ ፅዳት፣ የክረምት በጎ ፍቃድ አገለግሎት ላይ ትኩረት የሚደረግ ሲሆን፣ የመረዳዳት ባህልን የሚያዳብርና ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የፌዴራል ተቋማት አመራርና ሰራተኞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ትስስር የሚያጠናክር ነው ተብሏል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)