የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ ሊያደርግ ነው


ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ ወዲህ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን የአውሮፕላን በረራ ሊያደርግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ በትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱን ለማሻሻል የአውሮፕላን በረራ ፈቃድ መጠየቁን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃዱን ሰጥቶ ከዚህ ቀደም የመጀመሪያው ዙር በረራ መደረጉም ተመልክቷል፡፡
በዛሬው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በረራ ከ30 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሰራተኞች እንደተካተቱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡