በሀዲያ ዞን አሸባሪው ህወሓትን የሚቃወምና መከላከያን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – በሀዲያ ዞን የአሸባሪውን የህወሓት ጁንታን የሚቃወምና መከላከያ ስራዊትን የሚደገፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ክብር አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ የለም፣ የጦር መሳሪያ ከትግራይ ህፃናት ትከሻ ላይ ይውረድ፣ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ለህወሓት ያላቸውን ተቃውሞና ለመከላከያ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

በሆሳዕና ከተማ ዛሬ የተካሄደው ሰልፍ ከዞኑ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአስተዳደር አካላት፣ መካላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባላት መሳተፋቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡