ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት ሕፃናትን ለውትድርና መማገዱን ሊያወግዝ ይገባል- ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) – ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት ሕፃናትን ለውትድርና መማገዱን ሊያወግዝ እንደሚገባ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ጁንታው ሕፃናትን ለውትድርና እየተጠቀመ ስለመሆኑ በርካታ በማስረጃ የተደገፉ መረጃዎች እየወጡ መሆናቸውን ጠቁሟል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምታን የመረጠው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የዚህ አሸባሪ ቡድን ቅሪቶች ንፁሃን ልጆቻችንን ከፍተኛ አደጋ እያስከተለ ላለው አሳዛኝ ክስተት መጠቀማቸውን ሊያወግዝ ይገባል ብሏል።

የህወሓት ቡድን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ መፈረጁ ይታወቃል፡፡