አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ስብስብ ነው- አቶ ጌታቸው ባልቻ

አቶ ጌታቸው ባልቻ

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – አሸባሪው ትህነግ የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ስብስብ ነው ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገለጹ።

የአሸባሪው ትህነግ ስብስብ የመንግስትን ተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔን ያልተቀበለ፣ በተፈጥሮው ሰላም የማይፈልግና የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ መሆኑን አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል።

የአዳማ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።

አቶ ጌታቸው ባልቻ በአዳማ ከተማ የተካሄደውን የህዝቡን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክተው ትናንት  እንደገለፁት፣ የአሸባሪው ጁንታ ትህነግ ስብስብ በተፈጥሮው ሰላም የማይፈልግና የኢትዮጵያ ህዝቦችን በማጋጨት ዕድሜውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርግ ነው።

በአዳማ ከተማ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የኦሮሞ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ለመከላከያው ድጋፍ ማድረግ አለብን በማለት እየተደረጉ ካሉ ድጋፎች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው፣ አሸባሪው ጁንታ እየፈፀመ ያለው የኢትዮጵያ ህዝቦችን የማይወክል ሀገር ለማፍረስ የሚደረግ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ለመከላከያው ድጋፉን እየገለፀ የአሻባሪውን ድርጊት በማውገዝ ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ህወሓት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና አሸባሪውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ መካሄዱን ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡