የጠ/ሚ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሠራተኞችና ቋሚ ዘጋቢ ጋዜጠኞች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

ሐምሌ 19/2013 (ዋልታ) – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሠራተኞችና ቋሚ ዘጋቢ ጋዜጠኞች በጋራ አረንጓዴ አሻራቸውን በሚሊኒየም ፓርክ አሳርፈዋል።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ለህዝብ መረጃን ከማድረስ ባለፈ በእንዲህ አይነት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም በመሳተፍ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ያግዛል ተብሏል።

የችግኝ ተከላው ተሳታፊዎችም የተከሏቸውን ችግኞች እንድሚንከባከቡም ቃል ገብተዋል።

በሚሊኒየም ፓርክ በነበረው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የውጭ ቋንቋዎችና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩምን ጨምሮ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ሠራተኞች፣ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቋሚ ዘጋቢ የሆኑ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

(በአስታርቃቸው ወልዴ)