በትብብርና በመረዳዳት ጊዜያዊ ችግርን በዘላቂነት እንፈታለን – የአማራ ፋውንዴሽን

ሐምሌ 19/2013(ዋልታ) – በ2013 ዓ.ም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በወቅታዊ ችግር ተፈናቅለው በአርጎባ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፉን ያደረገው ፋውንዴሽኑ የምግብ እህል 400 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት በቦታው በመገኘት ለተፈናቃዮች አስረክቧል፡፡

ፋውንዴሽኑ “የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችንን በማጠናከርና በማስፋት ጊዜያዊ ችግርን በዘላቂነት መሻገር ይቻላል” ብሏል፡፡ ለድጋፉ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋናም ማቅረቡን ከደቡብ ወሎ ዞን አርጎባ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡