በቶኪዮ ኦሎምፒክ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – በቶኪዮ ኦሎምፒክ የአምስት ሺህ ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ውድድር ከመጀመሪያ ምድብ ሰንበሬ ተፈሪ 3ኛ፣ እጅጋየሁ ታዬ ደግሞ 4ኛ ሆነው ማጣሪያውን አልፈው ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡

ከሁለተኛው ምድብ ደግሞ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 1ኛ ደረጃ  በመያዝ ማጣሪያውን አልፋለች፡፡