በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አገኘች


ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ)
– በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ርቀቱን በ27 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ከ22 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ነው ያሸነፈው፡፡
በውድድሩ የተሳተፉት አትሌት በሪሁ አረጋዊ 27 ደቂቃ ከ46 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 4ኛ ደረጃ ሲያገኝ አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ደግሞ በ27 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ ከ3 ማይክሮ ሰከንድ 8ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡