በአሻባሪው ህወሀት የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚያስብ የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ሊካሄድ ነው

ሐምሌ 23፣ 2013 (ዋልታ) –  ሕወሓት የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚያስብ የትግራይ ተወላጆች የሚሳተፉበት የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት ነገ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

ህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ መሰየሙ ይታወሳል፡፡

ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ጋዜጠኛ አርዓያ ተስፋማሪያም የሻማ ማብራትና የጸሎት ስነ-ስርዓቱን አስመልከቶ ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጋዜጠኛ አረዓያ እንደተናገሩት፤ 53 የትግራይ ተወላጆች በቀናነት ሕዝባቸውን ለማገልገል በስራ ላይ ተሰማርተው በአሸባሪው ተገድለዋል።

በነገው እለትም የትግራይ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት እነዚህን ንጹሃን የሚያስብ የሻማ ማብራትና የጸሎት ፕሮግራም ይካሄዳል ብለዋል።

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት ምክንያት መንግሥት ወደ ህግ የማስከበር እርምጃ መግባቱ ይታወቃል።

መንግስት አሸባሪውን የህወሃት ቡድን አከርካሪ ሰበሮ መቀሌ ከተቆጣጠረ በኋላ ሕዝባቸውን በቅንነት ለማገለገልና ክልሉ ከገባበት ቀውስ ለማወጣት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋሙም ይታወሳል።

ጊዜ አስተዳደሩ ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሸባሪው ህወሓት በተላያየ መንገድ ጥቃት በመፈጸሙ ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወቃል።

ከመታሰቢያ መርሃ ግብሩ በኋላም በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት በኩል የእነዚህ ንጹሃን ሁኔታ እንዲከታተል መልዕክት እንደሚተላለፍ ጋዜጠኛ አርዓያ ተናግሯል።