ኤምባሲው በተለያዩ እስር ቤቶች የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መለሰ

ሐምሌ 25/2013 (ዋልታ) – በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በካቱንዱ፣ ኪያምቡ፣ ቲካ፣ ጊጊሪ፣ ጁጃ እና ሩይሩ ፖሊስ ጣቢያዎች የነበሩ 117 ዜጎችን ከኬንያ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ሀገራቸው እየመለሰ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በመጀመሪያው ዙር 60 ወጣቶች በሞያሌ በኩል ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን ቀሪዎቹ በሁለተኛ ዙር በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚመለሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡