ሚኒስቴሩ የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ላይ እየተወያየ ነው

ሐምሌ 24/2013 (ዋልታ) – የትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የ2014 ዓ.ም ዕቅድ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ ከዘርፉ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል::

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ በውይይቱ በሁሉም ተቋማት የታቀደው ከ10 ዓመቱ የብልፅግና እቅድ ተመንዝሮ የቀረበ መሆኑ የተረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በውይይቱ የተሟላ የጋራ አረዳድ እና መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡