በመተከል ዞን የፓዊ ወረዳ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

ሐምሌ 25/2013 (ዋልታ) – በመተከል ዞን የፓዊ ወረዳ ነዋሪዎቹ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ እየሰነዘረ ያለውን ድርጊት በማውገዝ ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት በድጋፍ በሰልፍ ገልጸዋል።

ቡድኑ ለዘመናት በህዝቦች መካከል የፈጠረውን የመለያየት ተግባር በማውገዝና አንድነትን በማጠናከር የኢትዮጵያ ህልውና ለማስጠበቅ እንደሚሰሩም የፓዊ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ላይ የሚገኘውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ዘብ እንደሚቆሙም ገልጸዋል።

ቀጠናው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚገነባበት በመሆኑ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከግብ እንዲደርሱ እንደሚሰሩ በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ የፓዊ ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተለያዩ የአገር አንድነትን የሚደግፉ እና አሸባሪው ህወሓትን የሚያወግዙ መልዕክቶች መተላለፋቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።