የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ተጀመረ


ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) –
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ጀመረ።
ጉባዔው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን መጨረሻው ይሆናል።
ምክር ቤቱ በቆይታው የአስፈጻሚውና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ለምክር ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የዘርፍ ተቋማት የሥራ አፈፃፀም ላይ እንደሚወያይ ተመላክቷል።
ምክር ቤቱ የዳኞች ሹመት፣ የአስተዳደሩን የ2014 በጀትና መሪ እቅድ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የመሬት ምዝገባ ጽህፈት ቤት ረቂቅ ዓዋጅ ላይ የሚወያይ ሲሆን በሚቀርቡ ሪፖርቶች ላይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የመስክ ግምገማ እንደሚያደርጉ ኢዜአ አመላክቷል።