በማይፀብሪ ግንባር አሸባሪው ቡድን አይቀጡ ቅጥታ እየተቀጣ ነው ተባለ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – ሠራዊቱ በማይፀብሪ ግንባር አሸባሪው የህውሓት ቡድንን አይቀጡ ቅጥታ እየቀጡት ይገኛሉ ሲሉ የ31ኛ አድዋ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ጀማል ከድር ተናገሩ፡፡

ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው ኮ/ል ጀማል ወደ ክፍለ ጦሩ ለተቀላቀሉ መሰረታዊ ወታደሮች ስለ ክፍሉ የአውደ ውጊያ ውሎ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

ህግ የማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ወቅት ክፍለ ጦሩ የአሸባሪውን የህውሓት ቡድንን እንዲፍረከረክ ካደረጉ የዕዙ  ክፍለ ጦሮች መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡

በማይፀብሪ በኩል ሀገሪቱን ለማዋረድና ለመጨፍጨፍ ፍላጎት እያሳየ ያለው አሸባሪው የህውሓት ቡድን ህፃናትን እና አዛውንቶችን ለውጊያ እያሰለፈ ቢገኝም  አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡