ሰማንታ ፓወር በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ ገንቢ ነበር – ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር

ሐምሌ 29/2013(ዋልታ) – የዩ ኤስ አይዲ ኃላፊ ሰማንታ ፓወር በኢትዮጵያ የነበራቸው ቆይታ ገንቢ ነበር ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ቃል አቀባይ ዲና መፍቲ ተናገሩ ።
ኃላፊዋ በሠላም ሚንስትር ሙፈርያት ከሚል በኢትዮጰያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ ተገልፆላቸዋል ብለዋል ።
ሰማንታ 1.5 ሚሊየን የኮቪድ ክትባት ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መምጣቸውም ተገልጿል፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በሣምንቱ የተከናወኑ ዲፕሎማሲ ሁነቶችን አስመልክት ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ ማብራሪያ ሠቷል።
በፖለቲካ ዲፕሎማሲ በኩል ም/ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት የአስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ኃላፊ ማርቲን ግሪፍት ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ ቢያውጀም አሸባሪው ህውት በተቃራኒው በክልሉ የሰብኣዊ ድጋፍ እንዳይ ደረስ ስለማስተጓጎሉ ገለጻ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።
170 የሰብአዊ ድጋፍ የያዙ የጭነት ተሸኮርካሪዎች በአሸባሪው ቡድን ታግተው እንደነበረም ገልጸውላቸዋል።
በአማራና አፋር ክልል የሽብር ቡድኑ ባደረገው ትንኮሳ 220 ሺህ ሠዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት መሆኑም
ተብራርቶላቸውል ተብሏል፡፡
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ 500 ኢትዮያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉም ተነግሯል፡፡
(በመስከረም ቸርነት)