የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ለሠራዊቱ የአንድ ወር ደመወዝ ለገሱ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዝ ለገሱ፡፡

ሀገርን ከወራሪ እየታደገ ያለውን የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት መደገፋችን አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት  የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች የገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ግንባር ድረስ በመዝመት የሀገሪቱን ክብርና ሉአላዊነት ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የገጠማትን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተና በኢትዮጵያዊነት  ስሜት በአንድነት በመቆም እንሻገረዋለን ብለዋል፡፡

ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን ሠራተኞቹ መግለጻቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም በድምሩ 475 ሚለየን ብር ገደማ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ለተለያዩ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡