ጠ/ሚ ዐቢይ በቶኪዮ በተገኘው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ነሀሴ 01/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአትሌት ለተሰንበት ግደይ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻች መልካም ዕድል ተመኝተዋል፡፡