ኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ አደረጉ

ነሐሴ 3/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልል ሴቶች 12 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ፤ የሱማሌ ህዝብ 11 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኦሮሚያ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊ ሰዲያ ኡስማን ሴቶች ልጆቻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ጋር እንዳዘመቱ አንስተው አሁን ደግሞ ድጋፋቸው በሁሉም ዘርፍ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

በተለይ ለአሸባሪው ህወሓት ሁሉም ህዝብ በሀገር ጉዳይ ላይ አንድ እንደሆነ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ከ19 ከተሞችና 21 ዞኖች የተውጣጡ ሴቶች ስንቁን እንዳዘጋጁ የጠቆሙት ሃላፊዋ ይህም ሴቶች በሀገር ግንባታ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

የሱማሌ ህዝብ ተወካይ ኡጋስ ሰሀለ በበኩላቸው የሱማሌ ህዝብ ለመከላከያ ያለውን አጋርነት ለማሳየት በገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።

(በመስከረም ቸርነት)