ነሃሴ 05/2013 (ዋልታ) – ወደ ትግራይ ክልል የምግብ ዕርዳታን ይዘው የገቡ የጭነት መኪናዎች 277 መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም አደርጎ ከትግራይ ከዋጣ በኋላ ህወሀት የእርዳታ እህል ለትግራይ ህዝብ እንዳይደርስ ሲያስተጓጉል መቆየቱ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ህወሐት ፀብ አጫሪነቱን ካቆሙ እርዳታ ወደ ክልሉ እዲደርስ ማንኛውንም አማራጭ እጠቀማለሁ ሲል መግለጹም አይዘነጋም፡፡