የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ሀገር የማፍረስ አጀንዳ በመታገል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አንዳይሻክር እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ

ነሃሴ 6/2013 (ዋልታ) – ከተለያዩ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ፣ታዋቂ ግለሰቦች እና ነጋዴዎች የተወጣጣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን ሀገር የማፍረስ አጀንዳ በመታገል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አንዳይሻክር የተለያዩ ስራዎችን ለማከናውን በዝግጅት ላይ መሆኑን ቡድኑ ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመገኘት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰቷል፡፡
የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ከ2004 ጀምሮ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ግብፅ እና ሱዳን በመሄድ የግድቡን የስራ ሂደት እና የጋራ ተጠቃሚነት በማስረዳት ቡድኑ ሀገራዊ ሀላፊነቱን መወጣቱን በመግለጫ አስታውቀዋል ፡፡
አሁን ላይም መንግስት ተነካ ብለን ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ተደፈረ በሚል ሀገራዊ ሀላፊነታችንን ለመወጣት እና ከህዝባችን ጋር በመሰለፍ ሀገራዊ ጥሪውን ለመቀበል ዝግጁ ነን ብለዋል ::
አክለውም አንዳንድ ምዕራባውያን እና ሚዲያዎቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የከፍቱትን ዘመቻ ለመመከት እና ለመቀልበስ የቻልነውን ሁሉ ለማድረግ እየሠራን ነው ብለዋል::
ለመከላከያ ስራዎት ፣ ለልዩ ሀይል እና ሚሊሻም ትልቅ ክብር አለን ድጋፍም እናደርጋለን ብለዋል ::
(በሜሮን መስፍን)