ህወሓትን በማውገዝ የትግራይ ህዝብ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪ ቀረበ

ነሀሴ 06/2013 (ዋልታ) – አሸባሪውን የህወሀት ቡድን በማውገዝ የትግራይ ህዝብ ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪ ቀረበ፡፡

የብጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አክሊሉ ታደሰ ፅንፈኛው የህወሀት ቡድን በስልጣን ዘመኑ የሀገርን ህልውና ወደ ጎን በመተው ራዕይ  የሌለው ትውልድ እንዲኖር በማድረግ እና እጅግ አምሮ የሚጠላውን ህዝብ ሲመራ የቆየ አሸባሪ ቡድን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን የትግራይን ህዝብ መደበቂያ አድርጎ እኩያ አላማ ሲያራምድ ቆይቷል  ያሉት አቶ አክሊሉ አሁን ላይ ግን የበሉበትን ወጨት ሰባሪ በመሆን ታፍራና ተከብራ የቆየችውን ታሪካዊ ሀገር ለማጥፋት ቆርጦ መነሳቱን የትግራይ ህዝብ በመረዳት በአንድነት ሀገራዊ መንፈስ  አሸባሪ ቡድኑን ሊመክት ይገባል ብለዋል፡፡

ትህነግ ስልጣንን ባለመጥገብ የሀገሩን ክብር በመናቅ እና  ለፖለቲካ ጥቅም ሲል ህፃናትን በማሰለፍ ከዛም አልፎ የውጭ ወራሪዎችን ምኞት ለማሳካት እየጣረ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በተለይም ወጣቱ ትውልድ የአሸባሪው ቡድን ሴራ በሁሉም አካባቢ የተዘረጋ መሆኑን በመረዳት አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል ሲሉ አቶ አክሊሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)