ዓባይ በረሃ ሌሊቱን ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ የትራፊክ መስተጓጓል አጋጥሟል

ነሀሴ 07/2013 (ዋልታ) – ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም በሚወስደው መንገድ ዓባይ በረሃ አካባቢ ልዩ ስሙ ፍልቅልቅ በሚባለው ስፍራ ላይ ሌሊቱን ባጋጠመ የድንጋይ መንሸራተት ናዳ  የትራንስፖርት አገልግሎት መስተጓጓል አጋጥሟል።

ይህን ችግር በቶሎ ለመቅረፍም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በስፍራው አሰቸኳይ ጥገና የሚያደርግ ግብረ ሃይል በመላክ  በስፍራው ከሚገኘው አሰቸኳይ ጥገና ቡድን ጋር በጋራ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡

ስራው ተጠናቆ መንገዱ ክፍት ሲደረግ የሚያሳውቅ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ገልጿል፡፡