የኦሮሚያ ክልል ለአፋር ክልል ተፈናቃዮች እህልና የመድሃኒት ድጋፍ አደረገ

ነሀሴ 07/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልል በአፋር ክልል አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሆን ከ2ሺህ ኩንታል የሚበልጥ እህልና የመድሃኒት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ዛሬ ድጋፉን ከኦሮሚያ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ዛሬ በሰመራ ከተማ ተረክበዋል።
ድጋፉ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት በርክክቡ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገልጿል።
ድጋፉ እርስ በርስ የመረዳዳትና አብሮነትን የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ችግርን በራስ አቅም መፍታት እንደሚያስችል ተመልክቷል።
በአፋር ክልል አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ከ76ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።