የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

ነሐሴ 10/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄዱ።

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ህይወቱን ለሚገብረው ሰራዊት ደም መለገሳቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው ሀገር የመታደግ ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከመከላከያ ጎን እንደሚቆሙም ተናግረዋል።

ሰራተኞቹ ደም ከመለገስ ባሻገር የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ እንዲውል አድርገዋል።

(በዙፋን አምባቸው)