የገንዘብ ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

ነሃሴ 10/2013(ዋልታ) – የገንዘብ ሚኒሰቴር “ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ፡፡
የገንዘብ ሚኒሰቴር ሰራተኞች እና አመራሮች ውዱን እና በገንዘብ የማይተመነውን ደም፤ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በመለገሳቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመው የህግ ማስከበር ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስም ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአሁኑ ወቅት ከሀገር መከላከያ ስራዊት ጎን በመሆን ሃገርን ለማዳን የተጀመረው የህልውና ዘመቻ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን መቀጠል እንዳለበት የሚኒሰቴሩ ሠራተኞች አሳሰበዋል፡፡