የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለሰራዊቱ ከ60 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

ነሃሴ 14/2013 (ዋልታ) – የጉለሌ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት ከ60 ሚልየን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ድጋፎችን አበረከተ፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አባዋይ ዮሐንስ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች 265 ሰንጋ በሬዎች 613 በግና ፍየሎችን እንዲሁም የተለያዩ ምግቦችን ጨምሮ በጠቃላይ  በአይነትና በገንዘብ 60 ሚልየን 1 መቶ 54 ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሰባት ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው የህወሀት ቡድን  በከፈተው ጦርነት  ሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳንወድ ተገደን የገባንበትን የህልውና ዘመቻ በአጭር ጊዜ አጠናቀን ፊታችንን ወደ ልማት የምናዞርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሲሉ አቶ አባዋይ አክለው ገልፀዋል፡፡

ወጥተን መግባታችን ፣ ሰርተን መብላታችን ፣ በእምነት መኖራችን ሀገር ስላለችን መሆኑን በመገንዘብ  ሊያጠፏት የተነሱትን የጥፋት ሀይሎች ተባብረን ልናጠፋቸው ይገባል ሲሉም  መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)