በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ

ነሐሴ 14/ 2013 (ዋለታ)— የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀትና  ህብረተሰቡን ከጎኑ በማሰለፍ ያገኘውን መረጃ መሰረት አድርጎ በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው  የክትትል ስራ ተከማችቶ የነበረ ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው ብረት በቁጥጥር ስር የማዋለው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እየሱስ ገዳምና ጦር ኃይሎች- ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኙ ሁለት ስፍራዎች ላይ ነው::

አሸባሪው የህዋሃት ጁንታ ቡድን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስና ሀገርን የማፍረስ እኩይ ተልዕኮውን ለማሳካት የተለያዩ የኢኮኖሚ አሻጥር መረቦችን ዘርግቶ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት ቀደም ሲል በተለያዩ 17 ቦታዎች ተከማችቶ በህዝብ ጥቆማና በክትትል የደረሰበትን በብዙ ቢሊየን ብር የሚገመት ብረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑምን መገለፁ ይታወሳል፡፡

ሰሞኑን ደግሞ ብረት አከማችተው የተገኙና በህገ-ወጥ ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በመጨረሻም ይህ ውጤት የተገኘው በህብረተሱ ትብብር በመሆኑ መረጃውን ላደረሱን ግለሰቦች ታላቅ ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ዜጎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሟቸው፡-

በነፃ የስልክ መስመሮች 987፣ 816፣ 991 እና በቢሮ ስልክ 0111110111 (አዲስ አበባ ፖሊስ)

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ  ወንጀል መከላከል ስልክ ቁጥር 0115524077 እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ስልክ ቁጥሮች 0115309027፣ 0115309231፣ 0115309077 መረጃውን በማድረስና አጥፊዎች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በታላቅ አክብሮት ይጠይቃል፡፡