ባለስልጣኑ የክረምት በጎ ስራ አስጀመረ


ነሃሴ20/2013(ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ የምግብ የመድሀኒት የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የክረምት በጎ ስራ አስጀመረ፡፡

የክረምት በጎ ፍቃ አገልግሎቱ ቤት እደሳ፣የአልባሳት ፣ ነፃ ህክምና ድጋፍ እና የደም ልገሳ መርሀግብር ያካታተተ ነው፡፡

ባለስልጣኑ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ንቅናቄውን ያስጀመረው በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 11 የአቅመ ደካማ ቤት እድሳትን በማስጀመር ነው፡፡

ከማዕከል እስከ ወረዳ በስሩ የሚገኙ ተቋማትና ሰራኞችን በማስተባበርም የ24 አቅመ ደካማ ቤቶችንም ለማደስ እቅድ ይዟል፡፡

በክረምት የበጎ ፍቃድ የተለያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ታመነ አጫሞ ከቤት እድሳቱ በተጨማሪ ለ1ሺ 103 ሰዎች የነፃ ህክምና አገልግሎት እንዲያኙ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

67 ሰዎችም የማዕድ ማጋራት ተጠቃሚ ሆነዋል ነው የተባለው፡፡

ባስልጣኑ በዛሬው እለት ለየወደቁትን አንሱ የአረጋውያ መርጃ ማዕከልም አልባሳት፣5ሺ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንም ድጋም አድርጓል፡፡

ባስልጣኑ የሀገርን ዳር ድንበር እያስከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት 15 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን በቀጣይም የደም ልገሳ መርሀግብርም እንደሚያናውን አስታውቋል፡፡

(በትእግስት ዘላለም)