በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ልኡክ ሽልማት ተበረከተ


ነሃሴ 20/2013 (ዋልታ) – በኬንያ-ናይሮቢ በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ በድል ለተመለሰው ልኡክ የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ።

በ18ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ በ3 ወርቅ፣ በ7 ብር እና በ2 ነሀስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች ከዓለም 4ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ላጠናቀቀው የአትሌቲክስ ቡድን ፌዴሬሽኑ የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል።

በሻምፒዮናው የወርቅ ሜዳሊያ ላመጣ 25 ሺህ ብር፣ የብር ሜዳሊያ ላመጣ 18 ሺህ ብር፣ የነሃስ ሜዳሊያላመጣ 10 ሺህ ብር ለዲፕሎማ 6 ሺህ ብር እና ለተሳትፎ 3 ሺህ ብር ለአሰልጣኞችና ባለሙያዎች እንዳስመዘገቡት ውጤት መሸለማቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።