የዋልታ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመለገስ ወሰኑ

 ነሀሴ 21/ 2013 (ዋልታ) – የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ለመለገስ ወስነዋል።
የኮርፖሬቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ንጉሴ መሸሻ ሰራተኞቹን ባወያዩበት ወቅት እንደተናገሩት ወቅታዊ የኑሮ ውድነት ሰዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነ ያለበት ወቅት መሆኑን እንደሚገዘቡ አስረድተዋል።
“እያንዳንዳችን የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩብንም፤ ችግሮች ሁሉ ኢትዮጵያን ከገጠማት የህልውና አደጋ በታች መሆናቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ንጉሴ፤ የሃገራችንን ሰላም ለመጠበቅ የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በየግንባሩ ለተሰለፈው የመከላከያ ሰራዊታችን አጋርነታችንን ማሳየት ይኖርብናል” ብለዋል።
የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሰራተኞች በበኩላቸው በተሰማሩበት የሙያ መስክ ሃገራቸው የተከፈተባትን ሃሰተኛ የሚዲያ ጦርነት እየመከቱ መሆናቸውን አስታውሰው ለሃገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን ለማሳየት ወስነዋል።
ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከመለገስም ባሻገር ደም ለመለገስ የወሰኑ ሲሆን ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖችም አልባሳት ለማሰባሰብ ቃል ገብተዋል።
(በነስረዲን ኑሩ)