የዳውሮ ዞን ለሰራዊቱ ከአስር ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ መሰብሰቡ ገለጸ

ነሀሴ 21/2021 (ዋልታ) – በዞኑ ለመከላከያ ሰራዊት ከአስር ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ መሰብሰቡ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተክሌ በዛብህ ገለጹ፡፡

የዳውሮ ህዝብ ዋና አስተዳዳሪ ጠላት ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ካለ ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸው ጎልቶና ጠንክሮ 6ኛ ዙር ሃገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ድሞክራስያዊ በሆነ ሁኔታ በማካሄድና ሁለተኛዉን ዙር የህዳሴ ግድብ በመሙላት የኢትዮጵያን ብልፅግና ጉዞ ማደናቀፍ እንደማይቻል ማረጋገጣቸውን አስታውሰዋል።

በዞኑ ዋና ከተማ በሚገኘዉ ታርጫ ስታዲየም በዛሬዉ ቀን ብቻ ቀድመዉ ርክብክብ የተደረጉት  169 በሬ፣ 6 ፍዬል፣ 7 በግ፣ 13 ኩንታል ኩኪስ፣ 19 ኩንታል በሶ፣ 8 ኩንታል በቆሎ፣ 13 ኩንታል ጤፍ፣ 259 ኪሎ ግራም ቅቤ እና ሁለት ሚሊየን ጥሬ ብር  ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ መላኩን የሃብት አሰባሰብ ኮሚቴ ገልጿል።

የዞኑ የሃብት አሰባሰብ ኮሚቴው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መግለጻቸውን ከዳውሮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መመሪያ ያገኘነው መረጃ አመላክተዋል፡፡