ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 5,726 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

ነሀሴ 22/2013 (ዋልታ) – ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡

ተመራቂዎቹ በዋናው ግቢ፣ በኦቶና ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም በታርጫ ግቢ በመደበኛ፣ በሳምንት መጨረሻ ቀናትና በምሽት መርኃግብር በመጀመሪያ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 3 ሺህ 304 ወንድና 1 ሺህ 964 ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

በተቋሙ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 185 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው እንደሚቀሩም ተገልጿል።

በምረቃው መርሐ ግብር ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡