የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሠራዊቱን እያበረታቱ ነው

ነሐሴ 23/2013 (ዋልታ) – የደቡብ ክልል የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በሁርሶ ኮንቲጀንት ወታደራዊ የስልጠና ማዕከል ሠራዊቱን እያበረታቱ ይገኛሉ፡፡

የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን የያዘው ልዑክ በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር በሁርሶ ኮንቲንጀንት ወታደራዊ ስልጠና ማዕከል በመገኘት ሰራዊቱን ለማመቃቃት ስራዎቹን እያቀረበ ነው፡፡

የክልሉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለሠራዊቱ የሞራል ስንቅ የሚሆኑ ሙዚቃዎች፣ ግጥሞችን ሽለላና ቀረርቶ የመሣሠሉ ስራዎች በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡

የሀገር መከታ ለሆነው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በቁሳቁስ እና በገንዘብ ከመደገፍ ባሻገር በአካል ተገኝቶ ወታደሩን የማበረታታት እና የማጀገን ስራ ትኩረት ተሠጥቶት እየተሠራ ነው የሚገኘው ሲል የደሬቴድ ዘግቧል፡፡