ማኅበሩ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረገ

ነሐሴ 23/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር አመራሮች፣ ሰራተኞችና አባላት ለመከላከያ ሠራዊት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

በተጨማሪም ማኅበር አመራሮች፣ ሰራተኞችና አባላት ” ደሜን ለሀገሬ ” በሚል መሪ ሃሳብ የደም ልገሳ አከናውነዋል።

ማህበሩ በዚህን ወቅት 70 ሺህ ብር ገንዘብና ስንቅ ለሰራዊቱ ድጋፍ አድርጓል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጳውሎስ ካሱ “ሽብርተኞች የሽንፈት ፅዋ ተጎንጭተው አገሪቷ ሉአላዊነቷ እስኪረጋገጥ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

መስማት አለማቻል ለሀገር ሉአላዊነትን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት ከመደገፍ አያግድም ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት፤ ማህበሩ በቀጣይም ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ከተመሰረተ ከ50 ዓመት በላይ አስቆጥሯል።