ከውጭና ከውስጥ የተደቀኑ ሀገራዊ ፈተናዎችን ለመወጣት ሁሉም ሙስሊም ዱዓ እና ሰደቃ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከውጭና ከውስጥ የተደቀነብንን ሀገራዊ ፈተና በድል እንድን ወጣ ሁሉም ሙስሊም በየመስጊዱ ዱዓ እና ሰደቃ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ በሀገራችን ላይ ያንዣበበውን መጥፎ ደመና አላህ እንዲያነሳልን ዱዓ እና ሰደቃ እንዲደረግ ሲሉ ነው የጠየቁት፡፡
በመሆኑም የየመስጊድ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች እና የሚመለከታችሁ ሁሉ በየተመቻችሁ ቀንና ሰዓት ወንድ ሴት፣ ወጣት ሽማግሌ፣ ሀብታም ድሃ፣ ህፃን አዋቂ ሳይባል በጋራ ስለ ሀገራችን ሠላም ዱዓ እንዲደረግ ሲሉም ሃይማኖታዊ መመሪያን ሰጥተዋል፡፡
ተግባራዊነቱም ከነገ ነሀሴ 25 ጀምሮ ችግሩ እስኪነሳ ፀሎቱ ቢቀጥል ጥሩ ይሆናል ብለዋል ማለታቸውን ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡