ህወሓት የኢኮኖሜ አሻጥርን እንደ አንድ አውደ ውጊያ አየተጠቀመበት ነው ተባለ

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – ህወሓት የኢኮኖሜ አሻጥርን እንደ አንድ አውደ ውጊያ አየተጠቀመበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  የዋጋ ንረትና የኢኮኖሚ አሻጥር ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ ጥናታዊ ጹሁፍ የቀረበ ሲሆን በህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተሰየመው ህወሓት የኢኮኖሜ አሻጥርን እንደ አንድ አውደ ውጊያ አየተጠቀመበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ሀገርን ለማፍረስ በሚሰሩ ሀይሎች እየተሰራ ያለውን ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመበጣጠስ የኑሮ ውድነትን መቀነስ የስፈልጋል ብለዋል።

ሀገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገንዘብ ነጋዴው ይሄን ጊዜ ከህብረተሰቡ ጎን በመሆን ሊያሳልፍ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ አምራቾች በበኩላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ የመጣው የጥሬ እቃ ዋጋ አንዱ የዋጋ ንረት ምክንያት ነው ብለዋል።

(በመስከረም ቸርነት)