በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርኃግብር ተካሄደ

በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች የማዕድ የማጋራት መርኃግብር አካሂደዋል፡፡

ተቋማት የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃግብርን ምክንያት በማድረግ በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ 450 ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

“መልካም ማድረግ እና ለሌሎች ማካፈል” በሚል በተካሄደው የማዕድ ማካፈል መርሃግብር ላይ የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር መስከረም ዘውዴ እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች መገኘታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡