የደቡብ ዕዝ አባላት ዝግጁነት

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – ‹‹በግንባር እየተዋደቁ ለሚገኙ ጓዶቻችን ደም ከመስጠት ባለፈ ከጎናቸው ቆመን የሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን›› ሲሉ በአገር መከላከያ ሰራዊት የደቡብ ዕዝ አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አስታወቁ።
ኢትዮጵያዊያን ኅብረታቸውን አጠናክረው በአንድነት ከተነሱ የማያሸንፉት የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ጠላት እንደማይኖር ነው አባላቱ ያስታወሱት፡፡
፻ አለቃ ሽመልስ መኮንን ከሌሎች የዕዙ አባላትና ሲቪል ሸራተኞች ጋር በመሆን የሽብር ቡድኑን ሕወሓት ለመደምሰስ በግንባር ለተሰለፈው ሰራዊት ደም ለግሰዋል።
በዚህ ወቅት በሰጡት አስተያየት “ራስን ለመስዋዕትነት አሳልፎ በመስጠት ኢትዮጵያን ማኖር የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው” ብለዋል።
የወታደር ተቀዳሚ እሴቱ ከራስ በፊት አገር የሚል መርህ እንደሆነ የተናገሩት ፶ አለቃ ብርሀኑ ጉርሜሳ በበኩላቸው፣ “ለአገር በጀግንነት እየተዋደቀ ላለው ጓዴ ደም መለገስ ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ቁርጠኛ ነኝ” ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያዊያን በግንባርም ሆነ በአካባቢያቸው ያለልዩነት ለአገር ኅልውና እያደረጉ ያሉት ተጋድሎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጥሪ ስለማቅረባቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡