ከ14 ሺሕ 662 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰድ

ነሐሴ 26 /2013(ዋልታ) – የዋጋ ንረት በማባባስ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር አድርገዋል በተባሉ 14 ሺሕ 662 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ገለፀ፡፡
የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ዴንጌ ቦሩ እርምጃው የተወሰደው አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በመጠቀም ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት የሚፍጠሩ ሰዎችን ለማስቆም መሆኑን ተናግረዋል።
እስካሁን 166 ሰዎች ላይ ክስ መመሥረቱን እና 14 ሰዎች ከ6 ወር እስከ 2 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ መደረጉን ነው ኃላፊው ያስታወቁት፡፡
መጪውን አዲስ ዓመት ሕብረተሰቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶች የንግድ ትርዒትና ዐውደ ርዕይ በክልል ደረጃ መዘጋጀቱም ታውቋል።
መረጃው ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።