በማይፀብሪ ግንባር የህወሓት ቡድን መደምሰስ

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የአሸባሪው ህወሓት ቡድን በዳባት በኩል ሰርጎ ለመግባት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም መደምሰሱን የግንባሩ አዛዦች ገልፀዋል።

በማይፀብሪ ግንባር የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ፣ የኦሮሚያ ሚሊሻ በሽብር ቡድኑ ላይ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት ዘመቻ በርካቶች መደምስሳቸውንና የተማረኩ የታጣቂው ቡድን አባላት መኖራቸውን ተናግረዋል።

አሸባሪው ቡድን የሚጠቀምባቸው የጦር መሣሪያዎች መማረካቸውም የተገለጸ ሲሆን፣ ቡድኑን ለመደምሰስ እየተካሄደ ባለው ዘመቻ ኅብረተሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡