ከለውጡ በኋላ የመጡ በረከቶችና የገጠሙ ፈተናዎች በምሁራን እይታ

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የአሁኑ ወቅት ሀገር የገጠማትን ችግር በጋራ መግታት የተቻለበት፣ የሀገር አንድነት የጠነከረበት እንዲሁም ህብረ ብሔራዊነት የጎለበተበት ጊዜ መሆኑን ምሁራን ገለፁ።

ምሁራኑ ከለውጡ በኋላ የመጡ በረከቶችና የገጠሙ ፈተናዎች ላይ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ገለፃ አደርገዋል።

በገለፃቸው ሀገሪቱ የገጠማትን ሀገር ለማፈራረስ የተነሳው ባንዳ እስከ ወዲያኛው ለማስወገድ የህዝቡ ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑን አንስተው፣ ፖለቲከኞች ሀገር ለመታደግ ያደረጉት ርብርብ የሚበረታታና የፖለቲካ ምህዳሩን የቀየረ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ከሽብርተኛው ቡድን ጎን የቆሙ ሀይላትን ለማሳፈርና ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል መሬት ላይ ያለውን እውነታ ማሳወቅ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የለውጡ ጉዞ በበርካታ ሳንካዎች የተወጠረ ቢሆንም፤ ይህንን ችግር ፈትቶ የሀገሪቱን ብልፅግና ያረጋግጣል ብለዋል።

(በዙፋን አምባቸው)