82 ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ መመለስ

ነሐሴ 28/2013 (ዋልታ) – ከሊባኖስ 82 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡

በተለያዩ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችንን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት ነው 82 ሴቶችን መመለስ የተቻለው፡፡

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ እና የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራሎች ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።