ነሐሴ 28/2013 (ዋልታ) ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ትጫወታለች።
በኳታር ለሚካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ የሚሳተፉ የአፍሪካ ሀገራትን ለመለየት የማጣሪያ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
ዋሊያዎቹ ጨዋታውን ለማካሄድ አስቀድመው ወደ ጋና ኬፕ ኮስት ያቀኑ ሲሆን፣ ትናንት ምሽት የመጀመሪያ ልምምድ ማድረጋቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኬፕ ኮስት ከተማ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላት ሲሆን፣ ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያ እና ጋና ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የሚያደርጉትን የማጣሪያ ጨዋታቸውን ታስተናግዳለች።
ከኢትዮጵያ እና ጋና በተጨማሪም ሞዛምቢክ ከኮትዲቯር፣ ዙምባብዌ ከደቡብ አፍሪካ፣ ሞሪታኒያ ከዛምቢያ፣ ናይጄሪያ ከላይቤሪያ፣ ቱኒዝያ ከኢኳቶሪያል ጊኒ በተመሳሳይ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ዛሬ እንደሚያካሂዱ ከካፍ ድረገጽ እና ሱፐር ስፖርት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://bit.ly/3vmjIZR
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
Tweets by walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!