የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ አቋም መግለጫ

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት ጦርነት ከመንግሥት ጎን ቆሞ የሽብር ቡድኑን እንደሚታገል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ሞክር ቤት አስታወቀ።
የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ፓርቲዎች ባደረጉት ምክክር የጋራ መግባባት ላይ በደረሱባቸው ጉዳዮች ላይ የወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል።
———————-‑——————————–
1. የእናት ጡት ነካሽ የሆኑት ሕወሓትና የእንጀራ ልጁ ኦነግ ሸኔ የተባሉ አሸባሪዎች በሕዝባችን እና በአገራችን የተከፈቱትን ጦርነት በጽኑ እናወግዛለን፡፡
2. የአገራችን ሉዓላዊነትን ለማስከበር ከአገር መከላከያ ሰራዊትና ከክልል ልዩ ሃይሎች ጋር አብረን በመሆን ለአገራችን እንዘምታለን፤
3. ምዕራባዊያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመዳፈር በእጅ አዙር የሚያደርጉትን ጦርነት በአስቸኳይ አቁሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲቆሙ ጥሪ እናቀርባለን፤
4. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጎረቤት አገር ሱዳንና ግብጽ በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ የሚፈጽሙትን ደባና ሴራ እንዲሁም የሚዳፈሩንን ሉዓላዊነት እንዲያቆሙ እንዲያደርግ ድርጅቱን በአጽንኦት እየጠየቅን የኢጋድ አባል አገሮችን በአገራችን ኢትዮጵያ እየተሰነዘረ ያለውን ወንጀልና ስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲያስቆሙልን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
5. በአገራችን እየታዬ ያለውን የዋጋ ንረትና የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችና ግለሰቦች መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር አድርጎ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፤
6. በችግራችን ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጎን ለተሰለፋችሁ ወዳጅ አገራት ህዝብና መንግስታት ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እስካሁን ላደረጋችሁልን ድጋፍ ምስጋና እያቀረብን ወደፊትም የተለመደ ትብብራችሁን እና ድጋፋችሁን እንዳይለየን እንጠይቃለን፤
7. ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተቃጣብንን ወረራና ጥቃት የተለመደውን የአበቶቻችንን ጀግንነትና ወኔ የተላበሰው መከላከያ ሰራዊታችንን እና የክልል ልዩ ሃይሎችን አኩሪ ድል እየተቀናጀንና ክብር መስዋዕትነት እየከፈሉ ጠላትን በማሳደድ ይገኛሉ፡፡በመሆኑም ከአብራክ የተከፈሉ ልጆቻችን ለመርደትና ጋሻ ለመሆን ያሳየው አኩሪ ታሪክ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም የአገራችንን ሰላም እስከሚረጋገጥ የጋራ ክንዳችንን በጋራ ለጋራ በማነሳሳት አለኝታ መሆናችንን ምናሳይበት ወቅት በመሆኑ ከጫፍ እስከ ጫፍ ድንበራችን እንድንጠብቅ የአካባቢያችንን ሰላም እንድንቆጣጠር በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
ነሐሴ 29 /2013 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ