የርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ መልዕክት

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል መሬትን በስነ ሥርዓት ማስተዳደር ከተቻለ ብቻ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡
ለ10 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሮሚያ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስልጠና የተጠናቀቀ ሲሆን በማጠቃለያው ለይ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሽመልስ ሕዝባችን የተገፋው መሬቱን ለመቀራመት ተብሎ ነበር ብለዋል።
በተለይ አርሶና አርብቶ አደሩ ቅድሚያ የሚሰጠው ተገልጋይ መሆን እንዳለበትና የከተማና የገጠር መሬት እኩል ትኩረት ተሰጥቶት እንዲመራም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በነሞምሳ አድማሱ