ከአሸባሪው ቡድን ስልታዊ ተራራን ያስለቀቀው ፌደራል ፖሊስ

ነሐሴ 30/2013 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ከጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሽብር ቡድኑ ይዞት የነበረውን ስልታዊ ተራራ ማስለቀቃቸው ተገለፀ።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ሰሜን ዳይሬክቶሬት የዲቪዥን 4 አባላት በቅንጅት ያስለቀቁት ቦታ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ የጎሀ ተራራና አካባቢ ነው።
ነሐሴ 27 እና 28 በተደረገ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በስፍራው መሽጎ የነበረው የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ሰብኣዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።
ፀረ ሕዝቡ ቡድን በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ የሕዝብና የመንግሥት ሃብትና ንብረት እየዘረፈና እያቃጠለ እንደሚገኝም የፌደራል ፖሊስ አባሎቹ ጨምረው ተናግረዋል።