የመስከረም ወር የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ

ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም ከጳጉሜን 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሁሉም ነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነሐሴ ወር በነበረበት እንደሚቀጥል ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡