የኢትዮጵያዊነት ቀን በየካ ክፍለ ከተማ

ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) ለኢትዮጵያዊነት ክብር እቆማለሁ እዘምራለሁ በሚል በየካ ክፍለ ከተማ የኢትዮጵያዊነት ቀን ተከብሯል።
ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና በቆራጥ ልጆቿ ተሻግራ ወደ ከፍታዋና ብልፅግናዋ ታመራለች ሲሉ የመርሀግብሩ ታዳሚዎች ተናግረዋል።
ከመከላከያ ጎን እንደሚቆሙ እና ለሀገራቸው በማንኛውም መልኩ ድጋፍ እንደሚያደጉ ገልፀው፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መጪው 2014 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆንም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
በትዕግስት ዘላለም